አይ.ዩ.አይ

አይ.ዩ.አይ (IUI)/ ኤ.አይ.ኤች(AIH)

 

አይ.ዩ.አይ (IUI)/ ኤ.አይ.ኤች(AIH) ምንማለትነው?

 

እርግዝናወይምፅንሰእንዴትነውበተፈጥሮአዊመንገድየሚፈጠረው?

 

አንድ ሴት እንድታረግዝ የግድ የወንድ ዘር ከብልቷ በማህፀን ጫፍ (ከታች የሚገኘው ጠባቡ የማህፀን ክፍል) አልፎ ወደ ማህፀን ከዛም ወደ አንደኛው የማህፀን ትቦ መግባት አለበት፡፡  የወንዱ ዘር ወደ ማህፀን ትቦ የደርሰውን እንቁላል ከእንቁልጢ (Ovary) እንደተለቀቀ ተገናኝተው  (አብዛኛውን ጊዜ እንቁላል በተለቀቀበት በኩል ባለው ትቦ) ፅንሰት ይፈጠራል፡፡

የማህፀን በር በተፈጥሮ ወደ ማህፀን የሚገባዉን የወንድ ዘር ቁጥር ስለሚገድብ ወደ ማህፀን ትቦ የሚደርሰው የወንድ ዘር ቁጥር ጥቂት ነው ፡፡ አይ.ዩ.አይ (IUI) የሚባለው የህክምና አይነት የሴቷ እንቁላል የሚፈለፈልበትን ጊዜ ገደብ ጠብቆ የወንዱን ዘር የሴቷን የማህፀን በር አሳልፎ ቀጥታ ማህፀን ውስጥ የማሰቀመጥ ሥራ ነው፡፡ የወንዱን ዘር የሴቷ የማህፀን ውስጥ ማሰቀመጥ ወደ ማህፀን ትቦ መሄጃውን ጊዜ ይቀንሰዋል፡፡  በዚህ ህክምና ወደ ማህፀን ትቦም ሆነ ወደ እንቁላሉ የሚደርሰው የወንድ ዘር ቁጥርም የተሻለ ይሆናል፡፡ ይህ ህክምና የአንድን ሴት የማረገዝ ወይም የመፀነስ እድል ለማሻሻል ሚደረግ ህክምና ነው፡፡

 

አይ.ዩ.አይ (IUI) ምን ግዜ ይጠቅማል?

 

ጥንዶች በተለየዩ ምክኒያቶች ልጅ የማግኘት እክል ሊገጥማቸው ይችላል፡፡ አይ.ዩ.አይ (IUI) ከነዚህ ቸግሮች መሀል ለተወሰኑት መፍትሄ ሊሆን ይችላል፡-

 

  • የሴት መሃንነት

 

አንዳንድ ሴቶች ላይ እንቁላል መፈልፈያ / መለቀቂያ ጊዜውን ጠብቆ የማይለቀቀበት (የማይፈለፈልበት) ሁኔታ ሲኖር ለነዚህ ሴቶች የእነቁላሉን ጊዜ የሚያስተካክል መድሐኒት ይታዘዝላቸዋል ፡፡ በ ተጨማሪም እንቁላል ሚፈለፈልበትን ጊዜ ገደብ ጠብቆ አይ.ዩ.አይ (IUI) ይሰራላቸዋል ፡፡

በተጨማሪም በማህፀን ላይ በተደረገ ቀዶ ህክምና ወይም በሌላ ምክኒያት ማህፀን በር ላይ ጠባሳ ሲኖር የወንዱ ዘር ወደ ሴቷ ማህፀን መግባት አይችልም በዚህ ጊዜ አይ.ዩ.አይ (IUI) ጠቃሚ ይሆናል፡፡

አንዳንድ መሀን ሴቶች የእነቁላል ጊዜ የሚያስተካክል መድሐኒት ሲታዘዝላቸው እነቁልእጢያቸው በአንድ ግዜ ብዙ እንቁላለችን ሊለቅ ይችላል ፡ በዚህ ጊዜ የአይ.ዩ.አይ (IUI) ህክምና የመፀነስ እድላቸውን ከፍ ያደርገዋል፡፡

 

  • የወንድ መሃንነት

 

አይ.ዩ.አይ (IUI) በብዛት የወንዱ ዘር ቁጥር ወይም እነቅስቃሴ ሲቀንስ ወይም ስንፈተ ወሲብ ሲያጋጥመው በተጨማሪም ዘር የመርጨት እክል ሲያጋጥመው ወይም ያልተለመደ የሽንት ትቦው ክፍተት ሲኖረው እንደ መፍተሄ ይጠቅማል፡፡

 

አይ.ዩ.አይ (IUI) እንዴት ነው ሚሰራው?

 

የወንዱ ዘር አንዴ ከተወሰደ በኋላ በላበራቶሪ ውስጥ እስከ ሁለት ሰዓት በሚወስድ ሂደት ታጥቦ ይወፍርና የወንድ ዘር ፈሳሹ ( ይህ ፈሳሽ አንዳንዴ ከበድ ያለ ቁረጠት ሴቷ ላይ ሊስያከትል ይችላል)  ይወገድለታል፡፡

አይ.ዩ.አይ (IUI) የሚሰራው የሴቷ እንቁላል የሚፈለፈልበትን ጊዜ ገደብ ጠብቆ ነው፡፡ የአይ.ዩ.አይ (IUI) ህክምና በአንፃሩ ቀላል እና አጭር ጊዜ ሚወስድ ህክምና ነው፡፡ አይ.ዩ.አይ (IUI) ታካሚዋ የምረመራ አልጋ ላይ ትጋደምና ሀኪሙ የማህፀን ጫፍ እንዲታየው ሰርጥ ማያ ወይም እሰፔኩለም (Speculum) የተባለ የሀክምና መሳሪያ ብልቷ ውስጥ ያስገባል፡ ከዛም ጠበብ ባለ የፕላስቲክ ትቦ (Catheter) በመጠቀም በላብራቶሪ ታጠቦ የተዘጋጀውን የወንድ ዘር ወደ ማህፀን ያሰገባል፡፡ ይህ ህክምና አብዛኛውን ጊዜ ህመም አልባ ቢሆንም አንዳንድ ሴቶች አነስተኛ የሆነ የሆድ ቁረጠት ያጋጠማቸዋል ፡፡

 

ምንያህልውጤታማነው?

 

የአይ.ዩ.አይ (IUI) ህክምና ስኬት በአንድ ሙከራ እስከ 20 በመቶ ሲሆን የአይ.ዩ.አይ (IUI) ን ውጤት ከሚወስኑት ምክኒቶች መሀል፡-

  • የሴቷ እድሜ
  • የመሀንነት ምርመራዎች
  • መሀንነትን ለማከም የሚሰጡ መድሀኒቶችን መጠቀም እና ልሎችም…..

 

የአይ.ዩ.አይ (IUI) ህክምና የጎንዮሽ ጉዳት

 

አንድ ሴት የአይ.ዩ.አይ (IUI) ህክምና ከማድረጓ በፊት መሀንነትን ለማከም የሚሰጡ መድሀኒቶችን ከወሰደች መንታ ወይም ሦስት ወይም ከዛ በላይ ልተፀንስ የምትችልበት እድል ሊኖር ይችላል ፡፡ የአይ.ዩ.አይ (IUI) ህክምና ማድረግ በሚወለደው ልጅ ላይ የትውልድ ጉድለት(Birth defects) አያመጣም፡፡ አይ.ዩ.አይ (IUI) ህክምና ከተደረገ በኋላ ኢፌክሽን ሊፈጠር የሚችልበት እድል ዘቅተኛ ነው፡፡