መካንነት ምንድነው

አለምአቀፍ የጤና ተቁዋም እንደገለፀዉ መካንነት ማለት ከአንድ አመት በላይ ያለ ፅንስ መከላከያ በተደረገ የግብረስጋ ግንኙነት ለመፀነስ ያለመቻል ነዉ፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በምእራብ አዉሮፓ 12-15 ፐርሰንት የሚሆኑ ባለትዳሮች በዚ ችግ ላይ እንዳሉ ይገለፃል፡፡ በአህጉራችን አፍሪካ ዉስጥም ከ 30 ፐርሰንት በላይ ሴቶች ማርገዝ በሚችሉበት እድሜ ላይ ይህ ችግር ሊያጋጥማቸዉ ይችላል ተብሎ ይገመታል፡፡

ከላይ እንደተገለፀዉ አንዳንድ ጊዜ ተጋቢዎች ከአመት በላይ ያለወሊድ መከላከያ ግንኙነት አድርገዉ ማርገዝ ባይችሉ እንኩዋን በአጋጣሚ ግን ከአመት በሁዋላ እርግዝና ሊፈጠር ይችላል፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከ 1-3 ፐርሰንት የወር አበባ ወቅት ፅንስ ሊፈጠር የሚችል ቢሆንም እድሜ በገፋ ቁጥር ግን የመፀነስ እድሉ እየቀነሰ እንደሚሄድ ያሳስባሉ፡፡

የመካንነትን ችግር ለመፍታት እንዲሁም የተለያዩ አማራጮችን ለመወሰን የስነልቦና ምክር አገልግሎት ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡

ለምክር አገልግሎት ለማግኘት ከወሰኑ ልጅ ለማግኘት ሌላዉ አማራጭ በጉዲፈቻ ልጅ ማሳደግ ወይንም ህፃናትን ከሚያሳድጉ ድርጅቶች ጋር በመስማማት ልጅ ወስዶ ማሳደግ የልጅን መኖር እርካታ የሚተካ ሌላ አማራጮች መሆናቸዉን ልናሳዉቃቹ እንወዳለን፡፡

ለመካንነት ህክምና ለማድረግ ወስነዉ ሲመጡ ምርመራዉ እንዲሁም አንዳንድ የላብራቶሪ ምመራዋች የተወሰነ ጊዜ ሊወስዱ እንደሚችሉ ሊታወቅ ይገባል በዚህም ሂደት ግዴታ የሆኑ በተለያዩ ጊዜ በተከታታይ በየደረጃዉ የሚሰጥ የተለያዩ የህክምና ሂደት ማለፍ ያለበት ህክምና መሆኑን ማወቅ ጠቃሚ ነዉ፡፡