- እርግዝናና የሰውነት ክብደት
- የሰውነት ክበድት እንዴት እርግዝና ላይ ተፅዕኖ ያደርጋል ፤
ብዙዎቹ ከክበድት በታች እና ክክበደት በላይ የሆኑና በጣም ወፍራሞች ለእርግዝና ችግር የለባቸውም፡፡ ነግር ግን እንዳንዶች እንቁላል የመለቀቅ (Ovulation) ችግር ይገጥማቸውዋል ፡፡
ክብድታቸው መጣም ዝቅተኛ የሆኑ የወር አበባ መዛበትና እንቁላል የመልቀቅ ችግር ይገጥማቸዋል ፡፡
የዚህ ዓይነት ችግር ያለባቸው ወደ ህክምና በመሄድ የችግሩን መንስኤ ማወቅና ማስተካከል ያስፈልጋል ፡፡
ከፍተኛ ክብደት ያላቸውም የወር አበባ መዛባትና እንቁላል የማመንጨት ችግር ሊገጥማቸው ይችላል ፡፡ አንዳንዶቹ ምንም አንቁላል የመልቀቅ ችግር ባይኖርባቸውም ለእርግዝና ተመጣጣኝ ክብደት ካላቸው ያነሰ ነው፡፡
ለእርግዝና ያለው ችግር እንቁላል አለማመንጫት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ወደ ህክምና የሚወስዱ ሁኔታዎች አሉ ፡ከከፍተኛ ክብደት በተጨማሪ እርግዝና ላይ ችግር ሊፈጥሩ የሚችሉ እንደ እንቅርት ፣ Insulin Resistance (ኢንሱሊን ማይጠቀም ወይም ማይቀበል) እና የስኳር በሽታ ያሉትን ማስታከካል ይገባቸዋል፡፡
- የሰውነት ክብደት እርግዝና ላይ ጤነኛ ህፃን ለማግኘት ችግር አለውን ?
ከፍተኛ ሰውነት ክበድት ከኤይ.ቪ.ኤፍ የሚገኘውን የእርግዝና ውጤት ዝቅ እንደሚያደርግ በጥናት ተረጋግጧል ፡፡
በእርግዝና ጊዜ የሚመጣ የስኳር በሽታ ፤ ደምግፊት አደገኛ ደረጃ ሊያደርስ ወደሚችል የደም ግፊት (Pre-eclampsia) ሊያጋልጥ ይችላል፡፡
ወፍራም ሴቶች በቀዶ ህክምና የመውለድ እድላቸው ከፍተኛ ነው፤ የሚወልዱትም ህፃኑ ላ የተፈጥሮ ችግርና በሚወለዱበትም ጊዜ ከፍተኛ ክበድት ይኖራቸዋል ፡፡
- ከፍተኛ ክብደት በወንዶች በመራባት ላይ ችግር አላቸውን ?
ወፍራም ወንዶች የሆርሞን መጠን ችግር ሊኖቸርባቸው ስለሚችል ይህም የወንድ ዘር ቁጥር ማነስ እንቅሰቃሴ መቀነስ ሁኔታ ሊፈጥር ይችላል፡፡
- ከእርግዝና በፊት ክብደት መቀነስ ያስፈልጋልን?
ክብደት የመቀነስ እርመጃ ከመወሰድ በፊት የህክማነ ባለሙያ ማማከርና እድሜናና ለመውለድ ችግር ሊሆኑ የሚችሉ የሚባሉ ሁኔታዎችን ከመቀነስ በፊት ማገናዘብ ያስፈልጋል ፡፡
ይህ እጢ ያለቸው ሴቶች ተጨማሪ ህክምና በማድረግ የስኳር ችግርን ለማስወገድ ወደ ባለሙያ መሄድ ያስፈልጋል ፡፡
ፖሊሲስቲክ ኦቫሪ ሲንድረም (PCOS) እና የሰውነት ክብድት ከካገጠመን ምን የተለየ ነገር ማድረግ አለብን?
ፖሊሲስቲክ ኦቫሪ ሲንድረም (PCOS) ወጣት ሴቶች ላይ የተለመደ ችግር ነው፡፡ ብዙዎቸ ሴቶች ይህ ችግር ያለባቸው ከመጠን በላይ ወፍራም እና ሰውነታቸው Insulin Resistant (ኢንሱሊን ማይጠቀም ወይም ማይቀበል) ችግር አለባቸው፡፡ ነገር ግን ይህ ችግር ያለባቸው ሁሉም ወፍራም ወይም ከመጠን በላይ ወፍራም አይደሉም፡፡
ይህ ችግር ያለባቸው ሴቶች ዝቅተኛ የሆን ካርቦሀይድሬት ያላቸውን ምግቦች በመብላት እና እስፖርት በመስራት የሰውነት ክብደትን በመቀነስ የወር አበባን ማስተካከል ይቻላል፡፡ በተጨማሪም ይህ ችግር ያለባቸው ሴቶች ሀኪም ጋር በመቅረብ መድሀኒቶችን በመውሰድ ይህን ችግር መታከም ይቻላል፡፡