ስለወንድ መሃንነት

ስለወንድ መሃንነት መታወቅ ያለበት  ፡-

 

መሃንነት ምንድን  ነው?

 

መሃነንት ባልና ሚስት ካለምንም የወሊድ መከላከያ በአንድ ዓመት ጊኤ በሚያደርጉት ግንኙነት አለመኖር ማለት ነው ፡፡

 

 • መሃንነት ምን ያህል በወንድ ምከንያት ሊሆን ይችላል ?

 

 1. መሃንንት በሴትም ሆነ በወንድ ምክንያቶች እኩል መጠን ሊከሰት ይችላል፤
 2. አንድ ሶስተኛው የሚሆነው በወንድም ሆነ በሴቶች ላይ የመገኙ ችግሮች ይችላሉ
 3. በተጨማሪም ምንመ ምክንያት ባለታወቀ ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል ፡፡

 

 • የወንድ መሃንነት እንዴት ይመዘናል ?

 

የወንድ መሃንት የሚመዘነው በህክምና በስነ ተዋልዶ (በዘር ፍሬው አፈጣጠር ፤ ብዛትና መጠን ) ነው ፡፡ በዚህ ሁኔታዎች ችግር ያለበት ከሆነ የሚመለከተው ሃኪም መታየት አለበት ሀኪሙም አስፈላጊውን የህክመና ሂደት ተከታትሎ ወደ ከፍተኛ ህክመና ሊመራ ው ይችላል፡፡

 

 • ወንዶችን መሃን የሚያደርጉ ምክነያቶች ?

 

 1. በአብዛኛው ምክኒያቱ አይታወቅም
 2. በዘር ፍሬ አካባቢ ባለ የደም ስር ችግር
 3. በተለያ ችግሮች መክንያት የመተላፋፊ ቱቦች መዘጋት
 4. በሚወስዱት መድሃኒቶች ምክነያት ሊሆን ይችላል፡፡

 

 • የደም ስር ችግር

 

ይህ ችግር በወንድ የዘር ማመንጫ አካባቢ ያለ የደም ስር መለጠጥ ሲሆን ይህም በሚደረጉ የህክመና ምርመራ ሊታወቅ ይችልላ፡፡ በብዛት ሊታይ እንዲሁም በሁሉቱም ሊያጋጥም ይችላል፡፡ የደም ስር ችግር በህክመና ማስተካከል ይችላል በሴቶች ላይ የሚያመጣው ችግር አይኖርም ፡፡

 

 • የመተላለፍያ ቱቦ ችግር

 

ይህ ብዙ ጊዜ በወንዶች ላይ የሚታይ ሲሆን ምክንያቶችም የወንድ  ዘር መተላላፊያ ቱቦ መቆረጥና ፤ አደገና የቁስለት ችግር የሚያመጡ የኢንፌክሽን በሽታዎች ናቸው ፡፡

 

 • በመድሃኒት የሚመጣ ችግር

 

የተለያዩ መድሃኒቶች የመውለድ ችግር ሊያመጡ ይችላሉ ፡፡ ነገርግን መድሃኒቶችን መውሰድበሚቋረጥበት ጊዜ እንደገና ወደ ማስረገዝ መመላስ ይችላል፡፡ ብዙውን ጊዜ ለዚህ ችግር የሚያጋልጡ መድሃኒቶች ከወንድ የሚመነጨው እንደጋንጥር እና የካንሰር መድሃኒት ሊሆን ይችላሉ ፡፡ የሚያመጡትመ ችግር የወንድ የዘር ፍሬ ቁጥር መቀነስ ሊሆን ይችላል ፡፡

 

 • የተለያዩ ችግሮች ያሉባቸውና እነዚህም ያልተወገዱ ከሆነ መውለድ ይቻላል ወይ ?

 

 

በእርግጥ ይቻላል ይህም የወንድ የዘር ፍሬ በቀጥታ ከዘር ፍሬ ማምረቻ በመውሰድና በዘመናዊ የህክመና ዘዴ በመጠቀም (IVF) መውለድ ይቻላል፡፡

 

 • እርግዝና ለማግኘት ስንት ጊዜ ግንኙነት መፈጸም ያስፈልጋል ፤

 

ለብዙ ጊዜ ግንኙነት ያቋረጡ ሰዎች የዘር ፍሬ ጥራታቸው ይቀንሳል ፡፡ ባልና ሚስት ቢያንስ በሳምንት ሁለት ወይም ሦስት ጊዜ ግንኙነት ማድረግ ይገባቸዋል ፡፡ ከሴቶች እንቁላል በሚፈጠርበት ጊዜ ባለው ስድሰት ቀናት ውስጥ ግንኙነት ማድረግ እርግዝና ሊከሰት ይችላል፡፡

 

 • አመጋገብ ለመራባት የሚፈጥርው ችግር ካለ

 

ውፍረት የወንድ የዘር እንዳይፈጠር ችግር ይፈጥራል ስለዚ ተመጣጣኝ የሆነ የሰውነት ውፍረት ሰውነትን ከተለያዩ ሁኔታዎች ሊታደጉ የሚችሉ ቫይታሚን ሲ ፤ ኢ እና የተለያዩ ፍራፍሬወቸ የወንድን የዘር ፍሬ ቁጥርና እንቅሰቃሴ ሊያሻሽሉ ይችላል፡፡ በተጨማሪም ተመጣጣኝ መግቦች መመገብ ሁኔታዎችን ሊለውጥ ይችላል ፡፡

 

 • ሲጋራና ለመዝናኛ የሚወሰዱ መድሃኒቶች ችግር

 

ሲጋራ ማጨስ የወንድን የዘር ፍሬ ጥራ ስለሚጎዳ ማስወገድ የተሸለ ነው እንዲሁም ለመዝናናት የሚወሰዱ መድሃኒቶች እንደማሪዋና ያሉ መደበኛመን የዘር ፍሬ ስራ ያስተጓጉላል ፡፡

 • አለባበስ

 

አለባበሳችን በዘር ፍሬ አካባቢ ከፍ ያለ ሙቀት የሚፈጥሩ ከሆነ የዘር ፍሬን ጥረት ሊቀንስ ይችላል ፡፡ ይህም በተቻለ መጠንአለባበሳችን በወንድ የዘር ፍሬ አካባቢ ሙቀት ሊፈጥሩ የማይችሉ ( ሰፋ የሉ ከጥጥ የተሰሩ የውስጥ ሱሪዎች) ቢሆኑ ይመረጣል፡፡