ፖሊሲስቲክ ኦቫሪ ሲንድረም (Polycystic Ovary Syndrome)
- ይህ ችግር እንዴት የመውለድ ችግር ያመጣል?
ምን ማለት ነው?
ፖሊሲስቲክ ኦቫሪ ሲንድረም (PCOS) ይህ የተለመደ የሴቶች የመውለድ ችግር ነው፡፡ ከ 5 – 10 % የሚሆኑ ሴቶች በዚህ ይጠቃሉ፡፡ ሴቶች ይህ ችግር ሲኖራቸው ከሚያሳዩት ምልክቶች ውስጥ የወር አበባ የመዛባት ችግር ፣ የፊት እና የሰውነት ፀጉር ማደግ፣ የሰውነት ክብደት መጨመር እና መካንነት ናቸው፡፡
- እንዴት ነው ፖሊሲስቲክ ኦቫሪ ሲንድረም (PCOS) የሚታወቀው?
ይህ በሽታ የሚታወቀው በሀኪም ምርመራ ፣ በላብራቶሪ እና በአልትራሳውንድ በሚገኘው ውጤት ነው፡፡
ይህ በሽታ ያለባቸው ሴቶች በአልትራሳውንድ የሚታዩት ነገሮች ተለቅ ያሉ ኦቫሪስ ወይም እነቁልጢ (Ovaries) ከብዙ ትንንሽ ሲስቶች ጋር ሲሆን በደም ምርመራ ሊገኙ የሚችሉት ደም ውስጥ የሚገኘው የስኳር መጠን መጨመር ፣ የኮለስትሮል መጨመር ወይም የወንድ ሆርሞን የሚገሉት መጨመር ኛቸው፡፡
- እንዴት ነው ፖሊሲስቲክ ኦቫሪ ሲንድረም (PCOS) ያለባቸው ሴቶች ሌላ የጎንዮሽ ምን ችግር አለባቸው?
አንድ የጎንዮሽ ችግራቸው የሚያያዘው ከተዛባ እንቁላል መልቀቅ (Ovulation) ጋር ነው፡፡ በዚህን ጊዜ ሰውነታቸው ውስጥ ያለው ኤሰተሮጅን (Estrogen) መጠን የጨምራል እና የማህፀንን የላይኛውን ክፍል ያጠነክረዋል ይህም ትክክል ይልሆነ የደም መፍሰስን ያመጣል፡፡ በዚህም የተነሳ ለማርገዝ ይቸገራሉ፡፡
ሜታቦሊክ ሲንድረም (Metabolic Syndrome) ፖሊሲስቲክ ኦቫሪ ሲንድረም (PCOS) ያለባቸው ሴቶች ላይ የሚታይ የተለመደ ችግር ነው፡፡ ለዚህም በሽታ ምልክቶቹ ከመጠን በላይ ውፍረት በተለይ ሆድ አካባቢ (ቦርጭ) ፣ ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን ፣ የደም ግፊት እና ኢንሱሊን የተላመደ የስኳር በሽታ፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ምክኒያቶች በሙሉ ደግሞ ለልብ በሽታ ትልቅ ምክኒያቶች ናቸው፡፡
ለፖሊሲስቲክ ኦቫሪ ሲንድረም (PCOS) ትልቁ ምልክቱ ከመጠን በላይ ወፍረት ነው፡፡
- መካንነት እንዴት ነው ፖሊሲስቲክ ኦቫሪ ሲንድረም (PCOS) ባለባቸው ሴቶች ላይ የሚታከመው?
- አንደኛው መንገድ እንቁላል መልቀቂያ ጊዜ (Ovulation) በሀኪም በታዘዘ መድሀኒት ማስተካከል፡፡
- ክብደት እንዲቀንስ በማድረግ ያልተዛባ የእንቁላል መልቀቂያ ጊዜ (Ovulation) እንዲኖር ማድረግ፡፡
- ለስኳር በሽታ የሚጠቅሙ መድሀኒቶች እንድትወስደ በማድረግ ሰውነት ኢንሱሊን በደንብ እንዲጠቀም በማድረግ የእንቁላል መልቀቂያ ጊዜ (Ovulation) እንዲሰተካከል ማድረግ፡፡
- አይ ቪ ኤፍ (IVF) ፖሊሲስቲክ ኦቫሪ ሲንድረም (PCOS) ያለባቸው ሴቶች እንዲያረግዙ ይረዳል ሌሎች ህክምናዎች ካልሰሩ፡፡
- እንዴት ነው ፖሊሲስቲክ ኦቫሪ ሲንድረም (PCOS) ለማርገዝ እየሞከረች ያልሆነች ሴት ላይ ሚታከመው?
መካንነትን ማከም ካልሆን እና ፖሊሲስቲክ ኦቫሪ ሲንድረም (PCOS) ን ማከም ከሆነ ፍላጎቱ ሊደረጉ ከሚችሉ ህክምናዎች መካከል
- የእርግዝና መከላከያ መውሰድና ሰውነት ላይ የሚወጡ ፀጉሮችንና ብጉሮችን መቀነስ ይቻላል፡፡
- የእርግዝና መከላከያ መድሀኒት በተጨማሪም የወር አበባን ያስተካክላሉ ፣ እርግዝና እንዳየፈጠር ያደርጋል እና የተወሰነ የካንሰር አይነትን ይከላከላል፡፡
- ከመጠን በላይ ያደገ የሰውነት ፀጉር እና ብጉርን የወንድ ሆርሞን ሊቀንስ በሚችል መድሃኒት ሊታከመ ይችላል፡፡
- ሌላው ደግሞ የሰውነት ክብደትን በማስቀነስ፡፡
እያንዳንዱ ህክምናዎች በሴቶቹ ፍላጎት የሚወሰን ነው፡፡