መካንነት ምነድን ነው
- መካንነት ማለት ከ አንድ አመት በላይ ያለ እርግዝና መከላከያ በተደረገ የግብረስጋ ግንኙነት ለመፀነስ ያለመቻል ነው ፡፡ ነግር ግን የሴት ዕድሜ 35 እና ከዛ በላይ ከሆነ መካን ለመባል የሚያስፈልግበት ጊዜ እስከ ስድስት ወር ነው ፡፡
ምን ያህል ሰው በዚህ ችግር ይታወካል
- መካንነት 10 -15% ጥንዶች ( አንድ ከሰባት ጥንዶች ) የሚታይ ችግር ነው ፡፡ ይህ ማለት ዕድሜያቸው ከ20 እስከ 45 የሆኑት ጥንዶች ላይ በጣም የተለመደ ችግር ነው፡፡ ብዙዎቹ ጥንዶች ሁሉም ነገር ጤና ሆነው በአንድ አመት ውስጥ ያረግዛሉ፡፡
የመካንንት ምክንያቶች ውስጥ
ሀ. የሴቶች
- ዕድሜ
የሴት ልጅ ዕድሜ ትልቅ ተፅዕኖ አለው ፤ በተለይ ወደ 30 እና 40 ዎቹ ስትደርስ ለጤነኛ ሴት በ20ዎቹ ዕድሜ ወይም የ30 መጀመሪያዎቹ አካበባቢ የማርገዝ ዕድሉ በየወሩ ከ25-30 % ሲሆን ነገር ግን በ 40 ዎቹ ውስጥ ያለች ሴት ግን የማርገዝ ዕድሉ 10% ወይም ከዚያ ያንሳል ፡፡
- የሴት ዘር ( እንቁላል) የመልቀቅ ችግር
እድሜዋ ለአቅመ ሔዋን የደረሰ ሴት በወር ውስጥ አንዴም እንቁላል (የሴት ዘር) ካለቀቀች የማርገዝ ችግር ያጋጥማታል ፡፡ ይህን ችግር ሊያመጡ ከሚችል ችግሮች የእንቅርት ህመም ሌላ የሆርሞን ችግሮች እና polcystic ovary syndrome (PCOS) የሚባል በሽታ ናቸው ፡፡
በተጨማሪ የወር አበባ በትክክል በየወሩ የማያዩ ሴቶች ይህ ችግር ያጋጥማቸዋል እንዲሁም ከመጠን በላይ ውፍረት መጨመር እና መቀነስ ይሆን ችግር ሊያመጣ ይችላል፡፡
- የማህፀን ቱቦ መጎዳት ወይም መዘጋት
የማህፀን ቱቦዎች ከማህፀን ጋር የተገናኙ ሲሆን የወንድ ዘር እና እንቁላል የሚገናኙበት ቦታ ነው ፡፡ የማህፀን ቱቦ መዘጋት ወይም መጎዳት መካንንት ወይም ከማህጸን ውጭ እርግዝናን ሊያስከትል ይችላል ፡፡
- የማህጸን ጫፍ ችግሮች
የማህጸን ጫፍ ችግሮች መካንንት ከሚያመጡ ችግሮች ውስጥ አንዱ ቢሆንም ነገር ግን ከስንት አንዱ ነው መካነንት የሚያመጣው ፡፡ የማህፀን ጫፍ ችግር ከሚያመጣው ተፅዕኖ መካከከል አንደ ፅንስ የማህፀን ግድግዳ ላይ ተለጥፎ እድገቱን እንዳይጀምር ያደርጋል ፤ ከተለመዱት የማህፀን ችግሮች መካከል የማኅጸን ጠባሳ ፖሎፒስ ፤ ፋይብሮይድ ወይም ትክክል ቅርጽ ያልያዘ ማህጸን ፡፡
- የሆድእቃ ችግሮች
ሆድዕቃ ችግሮች የሚባሉት ሆዳችን ውስጥ ያሉት የሰውነት ክፍል ( ኦርጋን)የሚሸፍን ጠባሳ ወይም Endometriosis (ኢንዶሜትሪዮሲስ)
Endometriosis (ኢንዶሜትሪዮሲስ)
ማለት ፡- ማህጸን ላይ የሚገኘው ቲሹ ( tissue ) በሌላ ቦታ ላይ ሲበቅል ነው ፡፡ ይሄ ቲሹ (pelvis) ፔልቪስ ውስጥ በሚገኘው በማንኛውም አካል ላይ ኦቫሪም ላይ ሊበቅል የሚችል ነው ፡፡
ለ. የወንድ መካንነት
- የወንድ ምከንያቶች
አንድ ሶስትኛው የሚሆነው የጥንዶች መካንነት ችግር በወንዶች ምከንያት ሲሆን ሌላው አንድ ሶሰትኛው የመካነንት ችግር ደግሞ በሁለቱም ጥንዶች በአንድ ላይ የሚከሰት ችግር ነው ፡፡ ወንዶች መካን የሚሆኑባቸው ምከንያቶች የወንድ ዘር አለመስራት እና ወይም፤የወንድ ዘር አለማመንጨት ናቸው፡፡
ሐ. ምክንያቶች ያልታወቀ የመሃን ችግር
ከ10 % እና ከዛ በላይ የሚሁኑ መካኖዎች የሚታወቅ ምክንያት የላቸውም ይህም ምክንያቱ ያልታወቀ የመሃን ችግር ይባላል፡፡ አልፎ አልፎም እንዚህ ችግሮች በህክምና ሊታገዙ ይችላሉ ፡፡